Dr. Tebabu Tessema Wubetu’s Debre Zeit years cover both his elementary and secondary Education. Those are the times where he made his best friends for life. Below are a collage of pictures that shows a snippets of the life and classmates of Dr. Tebabu Tessema Wubetu. He had a rich life in Debre Zeit like every where else he went.
[smartslider3 slider=”8″]
Here is a beautiful poem entitled ሐምሌ (July) written by the talented poet Befirdu to remember his friends. The red colours identifies the name of Dr. Tebabu Tessema Wubetu’s and Befirdu’s classmates. Befirdu weaves the classmates name in the poem which talks about the month of ሐምሌ (July).
ሐምሌ
ወራቶቹ ሁሉ ሔዱ እየተጠጋጉ
ዘር አልማው ለጋስ ወር ሐምሌ ቀርቧል ደጉ፡፡
ገና ከወዲሁ ሐምሌ እኔን ትዝ እያለኝ
ተስፋዬ አየለ ጌትነት ተሰማኝ፡፡
ለኔ ብቻም አይደል የሐምሌ ፀጋው
የዓለሙ ሁሉ የሺ ደስታ ነው፡፡
በፍቃዱ ባይሆን ባምላካችን ፀጋ
ማን ያመጣው ነበር ሐምሌን ከፍሎ ዋጋ፡፡
ዘለዓለም ተወዳጅ ከልብ የማይጠፋ
ሐምሌ እኮ ነው ደጉ የነብሳቶች ተስፋ፡፡
አዳነች ይላሉ ለምለሟ አገር
ሐምሌ ባይጐበኛት ምንትዋብ ነበር፡፡
የለምለም መስክ ናፍቆት ሲያሳጣ መድረሻ፡፡
ሐምሌ ነው ደጉ ወር የዚህ ችግር መርሻ
አዝመራና ከብቱ ሁሉም በየፊት፡፡
አደመ ሲደሰት ሐምሌን በማየቱ፡፡
ጋራህ ሸንተረሩ ሜዳው ሁሉ አበበ
አለምሸት ሊያገኝ በተስፋ ጠገበ
ደስታውን አሰፋ ሐምሌን እያሰበ፡፡
ከነአድማሱ ወዲያ ዓይን እስካየው ድረስ
የሚያውቅ ማን አለ ሐምሌ እንደሚሰጥ ቅርስ፡፡
ሐምሌ ባላባቱ የእግዚአብሔር ስዩም
እንዳንተ ቸር ለጋስ በምድር የለም፡፡
ገላን የሚያሳምር ውበትን የሚያድስ
ትልቅ ቸርነት ነው ይኽ የሐምሌ ቅርስ፡፡
የሐምሌን ውለታ ሊከፍሉ ሲጥሩ
ሐብቱስ ወዴት ሊገኝ መች ይበቃል ብሩ፡፡
ይህን አቢይ ወር አምላክ ሲፈጥረው
ለወራቱ ሁሉ አርጐ ጌታቸው
ለግርማው አጐልማሽ ነጐድጓድ ሰጠው፡፡
ውላለኝ ትዝታው የሐምሌ ፈገግታ
ከፊቴ አልሄድ አለኝ ጠዋትና ማታ፡፡
እንደምን አስቻለው እንዴትስ ሆነለት
ስለ ሐምሌ ፍቅር የሰው ልጅ ከማውራት፡፡
ኣፈወርቅ ለዛማ ባለ ትልቅ ግርማ
ይፈጠር ይሆን ወይ ሓምሌ አንተ የሚያማ፡፡
አባይነሽ አንች ዓለም ሰፊ ያለቅጥ፡፡
የሐምሌን ስጦታ እንደገንፎ ጉርሻ ታደርጊያለሽ ዋጥ፡፡
ጭለማ ቢሉህም ሐምሌ ብርሃኑን
ንጋት መቺ ታጣች የቀን ውጋጋን፡፡
ብርቱኳን ቢለማ ቢያምር ቢያቋምጥ
ለሐምሌ እጅ ነው ያበባው እምቡጥ፡፡
ስር ጓዋጡ ሁሉ በአረንጓዴ አማረ
ሁሉም መልክ አገኘ ተዋበ እያደረ፡፡
በሐምሌ ተካሰ ተጐድቶም አልቀረ፡፡
ያለፍነውን ድርጊት አይተህ ችግሩን
ተስፋችን ነህና ሐምሌ የኛ ካሳሁን
ከየሴም የመጣን ከነገዱ ሁሉ፡፡
ሐምሌን መሳይ ለጋስ አልበቀለም አሉ፡፡
ሜዳውና አፋፉ ፈካ ብሎ ሲያዩት
የገብረሃናን ፌዝ ይመስላል ያወሩት፡፡
ገበሬው ታተረ ታገለ ከእርፉ
በሩቅ ስለታየው የሐምሌ ወር ዘርፉ፡፡
ዩሴፍና አብርሃም የገቡት ከገነት
የሐምሌን አጋማሽ አልሰሩም ደግነት፡፡
አምላክ በችሎቱ ሲበይን በፍርዱ
ሐምሌን አንግሦታል በችሮታ ዘውዱ፡፡
መጣ እየከበደ ሐምሌ መስታዋት
በችግር ላይ ሁነን የማግኘት ጭላንጭል የምናይበት
ሂኬ ደቻሳ መልክአም ጉደታ በሙሉ ስም ነው
ከሐምሌት ሞክሼ አርጐ ሐምሌ ያለው ማነው፡፡
ሰለሞን ጥበቡ እንጂ ባይታይ ስህተቱ
ተሽሮ ውድቅ ሆኗል አዲስ ነገር የለም የሚለው ትንቢቱ፡፡
ታሪኩ አይዘርዘር ይቅርብን ማውራቱ
እኛ የምናውቀው ነጭ ያመጣው ጅቱ
ባይናችን ስናየው በከመ ቅጽበቱ
የሚያስደነፋን ነው ብር ብሎ መጥፋቱ፡፡
እንደዚሁም ደግሞ ሐምሌ በያመቱ
በአዲስነት እንጂ አይመጣም በጥንቱ፡፡
ወጥቼ ወርጄ ለፍቼ ያለረፍት
የሐምሌ ችሮታ ወጋየሁ በጥቅምት
ታደሰና ክብሩ የሐምሌ ሹመት
አሁንም መጣልን ሊያድለን ውበት፡፡
በሐምሌ ተስፋነት አውቀው ከታገሉ
መገኘቱ አይቀርም እንቁና አክሊሉ፡፡
ገበሬነኝ ፀላይ ባንተው ነው ተስፋዬ
በመላኩ ብለህ እንዳትቀና ሐምሌዬ፡፡
ግዛቸው ነብሳችን ውኃ እያጠጣህ
በዚህ ባንጣር በጋ እንዳለቁ አይተህ፡፡
ዕድለኛ ፍጡር ገበሬ ከሆን
ሕይወት ሳይኮበልል ሳይሄድ ሳይመንን፡፡
ለይኩን እያልን ሁሉንም አልፈን
መጪውን እንጠብቅ ሐምሌን ተስፋ አርገን፡፡
በዓይንዓለም ማየት በጣም መደሰት
ነገሩ ማሰላሰል ከልብ መጫወት
በሐምሌ ብቻ ነው ጣሙን ለሚያውቁት፡፡
የፏፏቴን ለዛ ሙዚቃ እየሰማሁ
ጥይቴን ደርድሬ ሽጉጥ አገንድሬ ጨፌውን እያየሁ
ኩራት ዘውዴን ጭኜ ጐርደድ ቆም እያልሁ
ፊቱን መለሰ እያልኩ ባምላኬ እየታመንሁ
ሐምሌ ያለማውን አዝመራ እየቃኘሁ
ገበሬ ስለሆንኩ ፊቴን እያፈካሁ
እድሜዩን በደስታ መግፋት እመኛለሁ፡፡
ከማጣት ወደማግኘት ለመድረስ በእግሬ
ፍጹም ስላቃተኝ በጋ ሙሉ ዞሬ
ሐምሌ ድረስልኝ ገላጋዩ አሻግሬ
ብዬ እዘምራለሁ ከልቤ ደፍሬ፡፡
በጐርፉ በውርጩ በኃይሉ አስፈራርቶ
ሽብሩ እንዲባባስ ነጐድጓድ አምታቶ
በመብረቅ ባትሪው የጠፋውን አይቶ
ተሾመ ለሁሉም ሐምሌ ክብር አግኝቶ፡፡
ታዲያ ይህን ለጋስ አስተካካይ ወር
ንጉሤ አለኝታዬ የማይል ፍጡር
አለ ወይ በምድር ከወፍ ከአዝርእቱ ከገበሬው ጋር፡፡
ከበፍርዱ በቀለ
ሰክ …………….. የተለየ የናፍቆት ሰላምታችን ይድረሳችሁ
ሐምሌ ……..ቀን ……ዓ.ም ዕሁድ ከ …በ….ሰዓት በምናዘጋጀው ስነበዓል ላይ እንድትገኙልን በታላቅ ትህትና እንለምናለን
ማህበሩ