Dedication

DEDECTED TO Dr. TEBABU TESSEMA WUBETU: YOU ARE WITH US ALWAYS DEEP IN OUR HEART

 

 

                                                                           

 

This website is dedicated to the loving memory of Dr. Tebabu Tessema Wubetu.  On top of his outstanding academic and professional accomplishments, Dr. Tebabu Tessema Wubetu was a truly beautiful person inside and out.

He was honest, respectful, considerate, humble, and remarkable human being. He dedicated his life to his family, friend’s, profession, democratic ideals and freedom loving people of Ethiopia and around the world.

He exemplifies the best in life. His true can-do spirit and deeds of accomplishing a lot with less and changing disadvantages into advantages is legendary. He is the symbol of the magic of Debre Zeit, the place where he grew up, and hence, this website is dedicated to celebrating him.

It is a great loss to all of us not to have him physically with us. However, we will continue to carry him in our hearts and minds. All of us who are fortunate to have met him and had an opportunity to be blessed with his friendship will dearly miss him. It hurts not to have him around to give us unreserved love, care, guidance, and encouragement to embrace the diversity of life like he did.

The Loving and caring Dr. Tebabu Tessema Wubetu, a dear Husband, father, grandfather, brother and a dear friend is gone, but will never be forgotten. With deep grief and broken heart, we bid him farewell and say REST IN PEAC Dear Dr. Tebabu Tessema Wubetu.

The End came suddenly and unexpectedly for Dr. Tebabu Tessema Wubetu

The video below is public announcement to the Ethiopian Community in U.K about the Sad news of the Passing of Dr. Tebabu Tessema Wubetu. Shortly before his passing, Dr. Tebabu Tessema Wubetu was heavily involved in fund raising for GERD in Newcastle. The unexpected news sent a shock wave to family and friends as no one expected it and everyone was making plans to spend quality time with Dr. Tebabu Tessema Wubetu after his well-deserved retirement. No one saw this coming. Incredibly painful to loss him. Those of us who are very close to him and are left behind without him say that “as usual you lead, and we will follow!”

GOODBYE POEM BY HIS DEAR FRIEND TEKOLA MEKONEN

 

 

 

Solomon Bisrat, Dr. Tebabu Tessema Wubetu’s nephew, shares with us a touching video of his fond memory of dear Uncle Dr. Tebabu Tessema Wubetu:

Dear Friend Benyam Tilahun fondly Recalling the unique circumstance under which he met and become friends with Dr. Tebabu Tessema Wubetu.

ጥበቡን ሳስታውሰው

ጥበቡ ውበቱን የማወቀው ሱዳን በስደት በቆየንበት ወቅት ነበር። ጥበቡ የሚያኮራ ጓደኛ፣ አስተዋይና ጥሩ መካሪ፣ ትእግስተኛ፣ ሁሉን በእኩልነት የሚያይ  እና ለሙያው ታማኝ የነበር። የጥበቡን ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን መቀበል ካቃታቸው ግለሰቦች አንዱ ነኝ።  በብዙ ጎኑ ለሰው እየተጨነቀ በተለይም እኔ ማድረግ ያለብኝን የጤና ክትትትል ሳይረሳ በተገናኘንና በተደዋወልን ቁጥር ሲያስታውስና ሲጠይቀኝ ሳይ የማስታወስ ችሎታው በጣም ይገርመኝ ነበር።

እንታገልበት የነበረው ድርጅታችን ችግር ገጥሞት አማራጭ በጠፋበት ወቅት ሁላችንም ወደ ሱዳን ተሰደን ነበርና በዚያን  ወቅት ገዳሪፍ ላይ ጥበቡን ተዋወኩት።  በነበርንበት የስደተኞች መጠለያ  ችግር የነበራቸው ብቻ ሳይሆን የጤና  ችግር የሚያሰቃያቸው ብዙ ስደተኞች ገዳሪፍ ነበሩ።  የጥበቡን የህክምና ባለሙያነት በትግል ሜዳ እያለን የሚአውቁ  ግለሰቦች አሁንም እንደድሮው የሱን እርዳታ ይጠይቁ ነበር።

የህክምና መሳሪያ ያልያዘ ሰው ማለት ወታደር ሆኖ ጠመንጃ እንደሌለው ግለሰብ አይነት ነውና ጥበቡ በጅጉ እውቀት እያለው እውቀቱን አለመጠቀሙ ያስቆጨው ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ገዳሪፍ የነበርነውን ስደተኞች ቡድን ይረዳ የነበረው (SCC) ሱዳን ካውንስል ኦፍ ቸርች ተራድኦ ድርጅት በወቅቱ የሕክምና ባለሙያዎች እጥረት ስለነበረ ለጥበቡ የሥራ እድል ተፈጠረለት። ጥበቡ ሥራ በመቀጠሩ  ሳይሆን በሙያው የጤና ችግርተኞችን ለመርዳት እድል በማግኘቱ በጣም ተደሰተ። ይህንንም በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምቼዋለሁ።

ዛሬ የስደት ኑሯችንን እንዴት እንገፋ እንደ ነበር ላወጋችሁ ስላልተነሳሁ በዚያ ላይ ጊዜዬን ማጥፋት አልፈልግም።  ግን በወቅቱ ስላጋጠሙኝና ስላስተዋልኳቸው የጥበቡ  በጎ ተግባራት  ላጫውታችሁ እንጂ። በጊዜው ብዙ የኤርትራ ስደተኞች ወደ ሱዳን ገብተው ስለነበር አዲስ የስደተኞች መጠለያ ተሰርቶ ነበርና ኤርትራውያንን  ብቻቸውን አስፍረዋቸው ነበር። ይህ በአብሮሃም የተከፈተው መጠለያ ካምፕ ት/ቤትና የጤና ጣቢያም ነበረው። የጤና ጣቢያውን ለማንቀሳቀስ  የሜዲካል ዶክተር ይፈልጉ ነበርና ጥበቡ በዶክተርነቱ  ተቀጠረ።

ጥበቡ ከስፍራው ሲደርስ በወቅቱ ጣቢያውን ያስተዳድሩ የነበሩት ኤርትራውያን  ጥበቡን ተቃውመው አማርኛ ተናጋሪ ዶክተር አይሾምብንም ብለው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው UNHCR ቢሮ በመሄድ ተቃውሟቸውን አሰሙ። በካምፑ ውስጥ የነበረው የ UNHCR  ወኪል ከተሰላፊዎቹ መካከል ተመራጮች ወደ ገዳሪፍ እንዲሄዱና አቤቱታቸውን እንዲያሰሙ  አደረገ። ተወካዮቹ ገዳሪፍ ያለው የ UNHCR  መስሪያ ቤት ድረስ በመሄድ አቤቱታቸውን አቀረቡ። የ UNHCR  ባለስልጣንም ተወካዮቹን “እናንተ ማን ያስተዳድር የሚለውን መምረጥ አትችሉም” ብሎ መለሳቸው። በዚህም ምክንያት ጥበቡ ስራውን ተረክቦ ማገልገሉን ቀጠለ። ባጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ የኤርትራ ስደተኞች የህክምና አገልግሎት በአጥጋቢ ሁኔታ ማግኘት በመቻላቸው እና ደከመኝ የማይል ዶክተር ስላገኙ ከተለያየ የስደተኞች ካምፕና አቅራቢያ ከሚገኙ ከተሞች ብዙ በሽተኞች በየቀኑ ይመጡ ነበር። በተጨማሪም ሱዳናውያን ሁሉ የሚመርጡት ክሊኒክ ሆነ።

አንድ ወር እንደሰራ ካምፑ ውስጥ የአስተዳደር ሰራተኛ ሆኖ የሚሰራው ኤርትራዊ  የጀብሃ ታጋይ የነበረ ጥበቡ እንዳይመጣብን ብሎ ሲያስተበበር ከነበሩት ግለሰብ አንዱ  ሚስቱ ምጥ ይዟት ስትጨነቅ ሲያይ ምርጫ ስላልነበረው ወደ ጥበቡ እርዳታ ፍለጋ መጣ። ግለሰቡ በእኩለ ሌሊት ጥበቡ መኖሪያ ድረስ በመሄድ  ባለቤቱ ምጥ ላይ መሆኗን እርዳታም እንደምትፈልግ ነገረው። ጥበቡ ግለሰቡ ይቃወመው የነበር መሆኑን ቢያውቅም፣ ምንም አይነት ማመንታት ሳያሳይ ወደ በሽተኛዋ ቤቱ አመራ።  እናም ያ ይቃወመው የነበረውን ግለሰብ ባለቤት በሰላም አዋለዳት ። በማግስቱ ከስራ በኋላ ጥበቡ ወደ አዋለዳት ሴት ቤት ጎራ ብሎ እንዴት እንደዋለች ሲጠይቅ ልጅቷ እያለቀሰች እንደዋለች ነገሩት። ሕፃኗን ሲመረምራት ሆዷ ተነፍቶ ሽንት መሽናት እንዳልቻለች ተገነዘበ። በምርመራ ሲያጣራ ሕፃኗ የሽንት መሽነዋ በልፋጭ መሰል ነገር እንደተዘጋና መሽናት እንዳልቻለች ተረዳ። በዚያ ያልተሟላ የህክምና መሳሪያ በሌለበት አስቸጋሪ ሁኔታ ሕፃኗን መሽኒዋን የዘጋውን ልፍጭ ስጋ በመቀስ ቆርጦ ማስተንፈስ አማራጭ ያልነበረው በመሆኑ በወቅቱ ጉድ የተባለውን ቀዶ ጥገና አካሂዶ ህፃኗን ክስቃይ አዳናት። በመቀጠልም ገዳሪፍ ያለውን አለቃውን በመደወል በአስቸኳይ መኪና እንዲላክለት አድርጎ በሽተኛዋ ህፃን ለተከታታይ ህክምና ወደ ገዳሪፍ ሆስፒታል እንድትሄድ አደረገ። በወቅቱ በሽተኛዋን ከወላጆቿ ጋር ወደ ገዳሪፍ እንዳመጣ የተላኩት ሹፌር እኔ ነበርኩና የነበረውን የሰውንም ሆነ የወላጆችን ደስታ በቅርብ የተመለከትኩት ጉዳይ ነው።

ጥበቡ በክሊኒኩ ውስጥ በጣም ተወዳጅ ከመሆኑ የተነስ ስደተኞች ብቻ ሳይሆኑ የሃገሩ ሰዎችም ወደ ክሊኒኩ በመሄድ የህክምና እርዳታ መጠየቅ ጀምረው ነበር። ጥበቡ አራት ወር በክሊኒኩ እንደሰራ ኡምሳቃጣ የሚባል ሌላ የስደተኞች የጤና ጣቢያ ተከፈተ። ይህ ደግሞ ለኤርትራዊም ሆነ ለኢትዮጵያ ስደተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ትልቅ ክሊኒክ ነበር። ገዳሪፍ የነበረው ሱዳናዊ የ UNHCR ዳሬክተርም ቀደም ሲል በጥበቡ ላይ የነበረውን ተቃውሞ በማስታወስ ጥበቡ አዲስ ወደተከፈተው ትልቅ የጤና ጣቢያ  እንደሚዛወር ነገረው። ይህንን የሰሙ አሁን ይስራበት የነበረው ጣቢያ ተጠቃሚ የሆኑ ኤርትራውያን ባለፈው አይመጣብንም እንዳላሉ ሁሉ ዛሬ ደግሞ አይሄድብንም ብለው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ጥበቡ በአራት  ወር ውስጥ ይህንን አይነት ለውጥ ማምጣት የቻለው ስራውን እና የፖለቲካ አመለካከቱን ለይቶ የሚያውቅ ግለሰብ ስለነበር ነው።

ጥበቡ ሁል ጊዜ አብረውት ለሚሰሩ የሚናገረው ነገር  “በሽተኛ በሽታው እንጂ ማንነቱ አይጠየቅም” የሚል ነበር። እስከዛሬ ድረስ በዚያ ቀውጢ ወቅት በጥበቡ የህክምና  አገልግሎት የተደረገላቸው ግለሰቦች ትልቅነቱን ማውሳት ብቻ ሳይሆን በድርጊቱ የብዙዎችን አመለካከት እንደቀየር እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ጥሩ ሰው አይበርክትም እንደሚባለው ጥበቡም ብዙ ያሰበውን ሳይጨርስ የተለመውን ሳያሳካ፣ የጡረታ እድሜውን እንደ ጀመረ፣ ወደ ዘላለማዊ ቤቱ አቀና። አምላክ በአጽደ ገነት እንዲያኖረው እየጸለይኩ፣ ለቤተሰብ በድጋሜ መጽናናትን እና ብርታትን ልመኝ። ጥበቡን መርሳት ከባድ ነው። እሱን መተካት ግን  ህልም ነው።

ብንያም ጥላሁን

ሲያትል ዋሽንግቶን።

A friend in need is a true friend indeed!

Jitendra Mistry is a dear lifelong friend of Dr. Tebabu Tessema Wubetu. Jitendra completed his high school at Debre Zeit with his dear friend Dr. Tebabu Tessema Wubetu. Dr. Tebabu Tessema Wubetu gave Jitendra two precious parting gifts when he was heading to Leicester, Uk to attend university there.  What is amazing is that the message shows true friendship, and the gift was delivered in a unique way. what is also remarkable is the value Jitendra accorded to the friendship and kept the gift for over forty years.

This is the first precious gift. The gift written in Amharic on a leaf states “your Friend, your brother who will never forget you, T. (Tebabu) W(Wubetu).

The second message to his parting dear friend Jitendra was a friendly advice to “remember or not to lose his memory of Ethiopia”.  The love of Ethiopia and being there for his friends any time they need help is in Dr. Tebabu Tessema Wubetu’s DNA.

Please Leave Your Memories

To reach you if needed